
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ለእማማ ዘውድነሽ መሸሻ #እመ በረከት የሚል የማዕረግ ስም ስትሰጣቸው ለረጂም ዓመታት በበጎ አድራጎት ሲሰሩ ስለቆዩና አሁንም ያንኑ ሥራ እየሠሩ ያሉ በመሆናቸው ነው።
የማዕረግ ስም የሰጧቸው የቤተ ክርርቲያን አባት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በተለይም መስከረም ፩/፳፻፲፭ ዓ/ም በእንጦጦ ደብረ ኃይል ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ያደረጉት ሰብአዊና ክርስቲያናዊ ተግባር ተጠቃሽ እንደነበር በደብዳቤው አውስተዋል።
እመ በረከት ዘውዲቱ መሸሻ ሌላውን ቀርቶ ከ17 በላይ አሳዳጊ ያጡ ልጆችን በጥበብና በሞገስ አሳድገው ለወግ ማዕረግ ለትዳር ያበቁ የዘመኑ አማናዊት እናት ናቸው።
መስከረም ፲፬/፳፻፲፭ ዓ/ም