የዓለም ባንክ የሥራ አላፊዎች የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማኅበርን ጎበኙ
የዓለም ባንክ የሥራ አላፊዎች ህዳር 26/2017 ዓ.ም ቁስቋም አካበቢ የሚገኘው ማዕከል በአካል ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የእማማ ዘውዲቱን ያለፉት 35 ዓመታት የሠሩት ሥራ በአካል ተገኝተው መመልከታቸው እንዳስደሰታቸው በመግለጽ የዓለም ባንክ በቀጣይ ሰራተኞቹን ሁሉ ይዞ በመምጣት እንደሚጎበኛቸው ቃል ገብተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የእማማ ዘውዲቱ በጎ ሥራ ለሌሎች ሴቶችና በጎ ለማድረግ የሚነሳሱ ሁሉ አርሃያነት ያለው ተግባር በመሆኑ ለሌሎች መነገር ያለበት አርሃያነታቸውን ሌሎችም መከተል እንዳለባቸው በማመናቸው በቀጣይ ከድርጅቱ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ አረጋግጠዋል፡፡
ስለጎበኛችሁን እናመሰግናል!!