ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን ካሉ ግንባር ቀደም እና ጠንካራ ተቋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን፣ በንግድ ስራው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሃላፊነቱንም በከፍተኛ ስሜት እንደሚወጣ በተግባር አሳይቷል። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ለእመበረከት ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል እያደረገ ያለው ድጋፍ እንደ ማሳያ ሊጠቀስ ይችላል።
የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ ለበርካታ ዓመታት የነገ ተስፋ ለሆኑ ህፃናት በፍቅር፣ በእንክብካቤ እና በጤንነት እንዲያድጉ በትጋት ሲሰራ የቆየ ድርጅት ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም ይህን በጎ ተግባር በማድነቅና በማበረታታት፣ በየዓመቱ የ12 ህፃናትን ሙሉ ዓመታዊ ወጪ በመሸፈን፣ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ እና የማዕከሉን ቤተ መጻህፍት በነፃ የዋይ ፋይ አገልግሎት እንዲጠቀም በማድረግ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በ2017 ዓ.ም ነሐሴ 30 ቀን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በቸገኙበት የኢትዮቴሌኮም ከፍተኛ አላፊዎች በአካል በመገኘት 1.4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ በጷጉሜን 1 ቀን ደግሞ 120 ደርዘን ደብተሮችን አበርክተዋል። በተጨማሪም በጷጉሜን 3 ቀን የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሁለት ሙክት በጎችን ድጋፍ አድርገዋል። ይህ ድርጊት ኢትዮ ቴሌኮም ለህፃናት ያለው አለኝታነት በተግባር ያረጋገጠበት ተግባር ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ዋና አገልግሎቶች
ከማህበራዊ ሃላፊነቱ ባሻገር
ኢትዮ ቴሌኮም ለሀገሪቱ እድገት እና ለህዝቡ ህይወት ምቹነት እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ድንቅ