
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም
የቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበርን በአካል በመጎብኘት የተለያዩ የልማት እና የህጻናት ድጋፍ ሥራዎችን ተመልክተዋል።
በዚሁ ውይይት ወቅት የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ አበባየሁ ፍቃዱ በሰጡት ገለጻ፣ ድርጅቱ እንዴት እንደተመሰረተ፣ በየደረጃው ያለፈባቸውን ሂደቶች እና በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ አብራርተዋል። በተለይም መምህራን በህጻናት እድገትና ትምህርት መዳበር ውስጥ ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
የድርጅቱ ሰራተኞች ለመምህራኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው በጉብኝቱ እንደደሰቱ ገልጸዋል።
መምህራኑም ጉብኝቱ አዲስ ግንዛቤ እንዳሰጣቸው በመግለጽ ወደፊት በክትትልና በድጋፍ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል፤ አንዳንዶቹም አንድ ልጅ ለማስጠናት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ የትብብር ግንኙነትን ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጾ ፕሮግራሙ በስኬት ተጠናቋል።