በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚኒሶታ ዴንቨር ኮሎራዶ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የድርጅቱ የክብር አምባሳደር በወቅቱ ባስላለፉት መልእክት እመ በረከት ዘውዲቱ ይህን ሁሉ ዘመን በጤና የኖሩት በበጎነታቸው ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ በጎ ሥራ እንዲቀና እና አብሯቸው እንዲሰራ እንዲተባበር ጥሪ አስተላልፈዋል።
ሌላዋ የድርጅቱ የክብር አምባሳደር ወ/ሮ ጸደይ እሼቱ(ሚሚ) እርሷም የእማማ ሕይወት ማርኳት ባለችበት በሀገረ አሜሪካ ዴንቨር ኮሎራዶ በጎዎች እያስተባበረች በመሆኑ ሁሉም አብሯት ከዚህ በጎ ነገር ጋር ቢተባበር በብዙ ሊጠቀም እንደሚችል ገልጻ በሀገረ አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንናትውለ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ አቅርባለች።
የድርጅቱ የቦርድ አመራር አካላት ብፁዕ አቡኑ ናትናኤል የድርጅቱ አምባሳደር ሆነው ለመስራት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቆ
የድርጅቱን የዓመቱ የበጎነት አዋርድ ሰጥቷቸዋል።

























































