ለማዕከሉ ህፃናት በበጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች የጤና ምርመራ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር በሽሮሜዳ ቁስቋም ለሚገኙ ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች ለሆኑ የማዕከሉ ህፃናት የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ የጤና ምርመራና የምክር አገልግሎት በበጎ ፈቃደኛ ዶክተሮች መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ተከናውኗል። በዚህ ፕሮግራም የህፃናቱ የጤና ምርመራ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣ የእድገት እና የአመጋገብ ሁኔታቸውም ምርመራ ተደርጎላቸዋል። ከምርመራው ጎን ለጎን…