አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም
የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር በሽሮሜዳ ቁስቋም ለሚገኙ ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች ለሆኑ የማዕከሉ ህፃናት የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ የጤና ምርመራና የምክር አገልግሎት በበጎ ፈቃደኛ ዶክተሮች መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ተከናውኗል።
በዚህ ፕሮግራም የህፃናቱ የጤና ምርመራ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣ የእድገት እና የአመጋገብ ሁኔታቸውም ምርመራ ተደርጎላቸዋል። ከምርመራው ጎን ለጎን በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ ምክር የተሰጠ ሲሆን፣ ተጨማሪ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህፃናትም በመለየት ወደሚመለከተው የጤና ተቋም እንዲሄዱ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
የበጎ ፈቃደኛ ህክምና ባለሙያዎቹ በሙያዊ ብቃታቸው በተጨማሪ ያሳዩት ሰብአዊነት የተሞላ አቀራረብ ለህፃናቱ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አበርክቶ አበረክቷል። ይህ ተግባር የህፃናቱን የጤና ጥበቃና ደህንነትን ለማጠናከር የተሟላና የተስተካከለ ዕድገት እንዲኖራቸው ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የህፃናቱን ጤና እና ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይም የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ለዚህ በጎ ስራ ጊዜያቸውን፣ እውቀታቸውን እና ጉልበታቸውን በመስጠት ላገለገሉን የህክምና ባለሙያዎች ለዶክተር የምስራች ጫኔ፣ለዶክተር ፀጋ ይልማና ለዶክተር ብሩክታዊት ከበደ በድርጅቱና በተጠቃሚ ህጻናቱ ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።