እናት ባንክ በእማማ ዘውዲቱ ሥም ካራ ቅርንጫፍን ሰየመ

By adminzewd

/// እናት ባንክ ዛሬ በእማማ ዘውዲቱ ሥም የከፈተውን ካራ ቅርንጫፍ እማማ ዘውዲቱ እና የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል። የባንኩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ሥራ ስያስጀምሩ እንደተናገሩት በወ/ሮ ዘውዲቱ ይህ ብራንች መከፈቱ ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸው ወደፊትም አብሮ ለመስራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል ክብር ለሚገባው ክብር ሰጥቷልና እናት ባንክን እናመሰግናለን ማን እንደእናት

እማማ ዘውዲቱ መሸሻ እመ በረከት የሚል የማዕረግ ስም ተሰጣቸው።

By adminzewd

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ለእማማ ዘውድነሽ መሸሻ #እመ በረከት የሚል የማዕረግ ስም ስትሰጣቸው ለረጂም ዓመታት በበጎ አድራጎት ሲሰሩ ስለቆዩና አሁንም ያንኑ ሥራ እየሠሩ ያሉ በመሆናቸው ነው። የማዕረግ ስም የሰጧቸው የቤተ ክርርቲያን አባት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ…

የአድራ አዋር መሥራች ድርጅታችንን ጎበኙ

By adminzewd

የአድራ አዋር መሥራችና ባለቤት ዲያቆን ፍሬው እማማ ዘውዲቱ እና ድርጅታቸውን ጎበኙ *///** መስከረም 17/2015 በዕለተ መስቀል በድርጅቱ የተገኙት ዲያቆን ፍሬውና ባልደረቦቻቸው በአሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ቅል ልብ ካላቸው ኢትዮጵያዊያን ያሰባሰቡትን ገንዘብ በድርጅቱ አካውንት እንደሚያስገቡ በመግለጽ ወደፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ለአንድ ሕጻን በሚለው ፕሮጀክት አብሮ ሰፊ ሥራ ለመስራት ቃል በመግባትና ሕጻናቱን በማበረታታት ግብኝታቸው አጠናቀዋል። እንዲሁም በዚህ ታላቅ…

የፈረስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለበጎ አድራጎት ተቋማት ድጋፍ ለማድረግ ከመረጣቸው ተቋማት መካከል የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናት ማሳደጊያ ሆኖ ተመርጧል።

By adminzewd

የፈረስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለበጎ አድራጎት ተቋማት ድጋፍ ለማድረግ ከመረጣቸው ተቋማት መካከል የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናት ማሳደጊያ ሆኖ ተመርጧል። *///* የደጋፉ መጠን የሚወሰነው የራይድ ትራንስፖርት ሲጠቀሙ በሚመርጡት ተቋማት የሚወሰን መሆኑን በመግለጽ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሁሉ ድርጅታችንን ቀዳሚ አድርገው እንዲመርጡ እና ከድርጅታችን ጋር በመሥራት የነገ ሀገር ተረካቢ ሕጻናት ለማገዝ የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ ተላልፏል። ይህ ታላቅ ተግባርን ለሚያከናውኑ የፈረስ…

እንኳን ደስ አላችሁ!

By adminzewd

እማማ ዘውዲቱ አንድ ተጨማሪ ልጅ በስርዓተ ቤተክርስቲያን ዳሩ እማማ ዘውዲቱ በግቢያቸው ከዚህ በፊት 22 ልጆችን ድረው የነበረ ሲሆን ይህ አሁን የዳሩት ልቻቸው እንዳልካቸው መኮንን 23 ሆኖ የተዳረ ነው

ህክምና

By adminzewd

ዛሬ ታህሳስ 24/2014 ዓም በዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ መልጃ ማዕከል ውስጥ ከቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የተወጣጡ ዶክተሮች የነጻ ህክምና ካምፔን አደረጉ ***/// በዚህ ህክምና 35 ህጻናትና ወላጆቻቸው እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ ህጻናትና ሰራተኞች በድምሩ ወደ120 ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል:: የህክምና ቡድኑ አስተባባሪ ዶ/ር ምስክር ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት በእማማ ዘውዱቱ ሥራ መደነቋንና በቀጣይም አብረን ለመስራት ዝግጁ…