አዲስ አበባ | ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ላሉ ተቋማት አርዓያና ምሳሌ የሆነው የዘወትር አጋራችን ኢትዮ ቴሌኮም በማህበራዊ ኃላፊነት መወጣት መርሃ ግብር ለድርጅታችን ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የኩባንያው ሀላፊዎችና ሰራተኞች በማዕከላችን በመገኘት የጉብኝትና የስጦታ መርሃ ግብር ያካሄዱ ሲሆን ይህ አይነት ድጋፍ ኩባንያው ከመደበኛ አገልግሎት መስጠት ባሻገር ለወገን ደራሽነቱን አዲስ አመትን በበጎነት በሚል መሪ ቃል መነሻነት ድጋፉን አበርክተዋል፡፡
ድጋፉ በድርጅቱ እንክብካቤና ድጋፍ ለሚያገኙ ህፃናት የትምህርት ሂደትን ለማጠናከር፣ የትምህርት እድላቸውን ለማስፋት እና የተሻለ የወደፊት እድል እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ነው።
በድጋፉ የተካተቱት የትምህርት ቁሳቁሶች ህፃናቱ በትምህርታቸው የሚያስፈልጓቸውን መሰረታዊ ግብዓቶች በማሟላት በትምህርት ውጤታማነታቸው ላይ አዎንታዊ ሚና ይኖራቸዋል። በተጨማሪም የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ድርጅቱ ለህፃናቱ የሚሰጣቸውን የተለያዩ ድጋፎችና አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያግዝ ነው።
የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር አመራር፣ ሰራተኞችና ህፃናቱ ኢትዮ ቴሌኮም ላደረገው የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቀረቡ።
ድርጅቱ እንደገለጸው፣ እንደዚህ ያሉ የተቋማት ድጋፎች ህፃናት በተሻለ ሁኔታ እንዲኖሩ፣ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና የራሳቸውን ብቃት በማሳደግ ለሀገራቸው ጠቃሚ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያበረታቱ ናቸው።
ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha
“ለህፃናት የሚደረግ ድጋፍ ለነገ ተስፋቸው ስንቅ ነው!”
ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር

















