አዲስ አበባ | ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር ጋር ባለው ትብብር መሰረት በድርጅቱ የሚገኙ ህፃናትና ሰራተኞችን በመጎብኘት የህክምና አገልግሎትና ድጋፍ ሰጠ፡፡
የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች በድርጅቱ በአካል በመገኘት ለህፃናቱና ለሰራተኞች የጤና ምርመራ እና የህክምና አገልግሎት አከናውነዋል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የህክምና ምርመራዎች በማድረግ ከጤና ሁኔታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምክርና መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዕለቱ የህክምና ቡድኑ የላብራቶሪ ምርመራን ጨምሮ ለህፃናቱ እና ለሰራተኞች አስፈላጊ የሆኑ የጤና ምርመራ አገልግሎቶችን ሰጥተዋል፡፡ ይህም የህፃናቱን ጤና በመከታተል፣ የጤና ችግሮችን ቀድሞ ለመለየትና ተገቢውን የህክምና እርምጃ በወቅቱ ለመውሰድ የሚያግዝ አስፈላጊ ድጋፍ ነው፡፡
የድርጅቱ መስራች እመበረከት ዘውዲቱ መሸሻም ለህክምና ብድኑ ከዚህ በፊት ላደረጉት አሁንም ላበረከቱት ድጋፍ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈው ወደፊትም ድጋፋቸው እንዳይለይ ማሳሰቢያ የሰጡ ሲሆን የህክምና ቡድኑም ድርጅቱ ለሚያደራጀው የመጀመሪያ ህክምና መስጫ የውስጥ ክሊኒክ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶችን ለመስጠትና ቅድመ መከላከል ላይ ስልጠና እንደሚያዘጋጁ ቃል በመግባት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ማህበራችን ለቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታልና ለህክምና ቡድኑ ለህፃናቱና ለሰራተኞች ያደረጉትን የጤና አገልግሎት፣ ትብብርና ድጋፍ የላቀ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን እንዲህ ዓይነት ትብብሮች የህፃናትን ጤናና ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆናቸው በቀጣይም የጋራ ትብብሩ እንዲጠናከር እንደሚሰራ አሳውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha
“ጤናማ ህፃን፣ ለተሻለ ነገ!”
ዘውዲቱ መሸሻ የሕፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር




