እናመሰግናለን

By adminzewd

​ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን ካሉ ግንባር ቀደም እና ጠንካራ ተቋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን፣ በንግድ ስራው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሃላፊነቱንም በከፍተኛ ስሜት እንደሚወጣ በተግባር አሳይቷል። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ለእመበረከት ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል እያደረገ ያለው ድጋፍ እንደ ማሳያ ሊጠቀስ ይችላል። ​የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ ለበርካታ ዓመታት የነገ ተስፋ ለሆኑ ህፃናት በፍቅር፣ በእንክብካቤ እና በጤንነት እንዲያድጉ…

የዓለም ባንክ

By adminzewd

የዓለም ባንክ የሥራ አላፊዎች የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማኅበርን ጎበኙ የዓለም ባንክ የሥራ አላፊዎች ህዳር 26/2017 ዓ.ም ቁስቋም አካበቢ የሚገኘው ማዕከል በአካል ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የእማማ ዘውዲቱን ያለፉት 35 ዓመታት የሠሩት ሥራ በአካል ተገኝተው መመልከታቸው እንዳስደሰታቸው በመግለጽ የዓለም ባንክ በቀጣይ ሰራተኞቹን ሁሉ ይዞ በመምጣት እንደሚጎበኛቸው ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእማማ ዘውዲቱ…

እማማ ዘውዲቱ ድርጅት ውስጥ ያደጉ አራት ልጆችን አስመረቀ

By adminzewd

የእማማ ዘውዲቱ ድርጅት ጥቅምት 6/2015 ዓ.ም በድርጅቱ ውስጥ ያደጉ አራት ልጆችን አስመረቀ በዕለቱ ከተለያዩ ተቋማት የተመረቁት ተማሪዎች 2 በማስተርስ 2 ደግሞ በዲፕሎማ የተመረቁ ናቸው ተማሪዎቹ በምረቃቸው ወቅት ለእዚህ ክብር ያበቃቸውን የእማማ ዘውዲቱ እና የድርጅቱን ድካም አቅም በፈቀደ ሁሉ ለመመለስና ሀገራቸው በመጥቀም ብድራቸውን ለመመለስ እንደሚተጉ ተናግረዋል።

እናት ባንክ በእማማ ዘውዲቱ ሥም ካራ ቅርንጫፍን ሰየመ

By adminzewd

/// እናት ባንክ ዛሬ በእማማ ዘውዲቱ ሥም የከፈተውን ካራ ቅርንጫፍ እማማ ዘውዲቱ እና የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል። የባንኩ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ገነት ሥራ ስያስጀምሩ እንደተናገሩት በወ/ሮ ዘውዲቱ ይህ ብራንች መከፈቱ ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸው ወደፊትም አብሮ ለመስራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል ክብር ለሚገባው ክብር ሰጥቷልና እናት ባንክን እናመሰግናለን ማን እንደእናት

እማማ ዘውዲቱ መሸሻ እመ በረከት የሚል የማዕረግ ስም ተሰጣቸው።

By adminzewd

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም ለእማማ ዘውድነሽ መሸሻ #እመ በረከት የሚል የማዕረግ ስም ስትሰጣቸው ለረጂም ዓመታት በበጎ አድራጎት ሲሰሩ ስለቆዩና አሁንም ያንኑ ሥራ እየሠሩ ያሉ በመሆናቸው ነው። የማዕረግ ስም የሰጧቸው የቤተ ክርርቲያን አባት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስም ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና የደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ…