ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር ለትምህርት ዕድገት፣ ለእውቀት ሽግግርና ለንባብ ባህል ማዳበር ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት፣ ለወረዳ 01 ወጣት ማዕከል የተለያዩ ይዘቶችን የያዙ መጻሕፍትን ድጋፍ አደረገ።
ማህበሩ ያደረገው ይህ የመጻሕፍት ድጋፍ የወጣት ማዕከሉን የንባብ ባህል ከማሳደግ ባለፈ፣ ለህፃናት፣ ለተማሪዎች፣ ለወጣቶችና ለሌሎች የንባብ ወዳጆች የእውቀት ምንጭ እንዲሆን የሚያግዝ ነው።
ድጋፉ የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን የሚሸፍኑ መጻሕፍትን ያካተተ በመሆኑ የወጣት ማዕከሉን አገልግሎት ለማጠናከር፣ የንባብ ፍላጎትን ለማበረታታትና የማኅበረሰቡን የእውቀት አድማስ ለማስፋት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር እንደ የበጎ አድራጎት ተቋም ለህፃናት፣ ለቤተሰብና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅሙ የልማትና የማኅበራዊ ድጋፍ ተግባራትን በማከናወን ለማኅበረሰቡ ዘላቂ ጥቅም ለማበርከት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየ ይገኛል።
እውቀትን ማጋራት ለተሻለ ነገ መሠረት ነው!
ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር
ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha

