አዲስ አበባ | መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም

ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር በበጋ ወቅት በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል የተቀላቀሉ ወጣቶችን በማህበሩ ያሉ ህፃናትና ሰራተኞች ጋር ለማስተዋወቅ የትውውቅ መርሃ ግብር አዘጋጀ።

በመርሃ ግብሩ ወቅት ወጣቶቹ ስለ ማህበሩ አመሰራረት፣ ዓላማ፣ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና የሥራ መስኮች እና ለህፃናትና ለቤተሰቦች የሚሰጣቸውን ድጋፎች አጠቃላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በተጨማሪም በበጎ ፈቃድ ቆይታቸው የሚያከናውኗቸው ተግባራት፣ የሥራ ኃላፊነታቸው፣ ከህፃናቱ ጋር ሲገናኙ ሊከተሏቸው የሚገቡ የህፃናት ጥበቃና ደህንነት መርሆዎች እንዲሁም የማህበሩን የውስጥ ደንቦችና የሥራ ሥነ-ምግባር በተመለከተ ገለጻ ተሰጥቷል።

የበጎ ፈቃደኞቹ ተሳትፎ ህፃናቱ በትምህርት፣ በመዝናኛ፣ በግል እድገትና በሌሎች የዕለት ተዕለት ተግባራት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያገኙ ከማገዝ ባሻገር፣ ወጣቶቹም የበጎ ፈቃደኝነትን እሴት በተግባር እንዲለማመዱ እና ለማህበረሰቡ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ዕድል ይፈጥራል።

ማህበሩ በቀጣይም ወጣቶችን በበጎ ፈቃደኝነት በማሳተፍ የህፃናትን ደህንነትና እድገት ለማጠናከር እና የበጎ ፈቃደኝነት ባህልን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ይቀጥላል።

ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦

Websit: https://zewditumeshesha.org/

Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk

YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION

TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha