አዲስ አበባ | ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም
ዘውዲቱ መሸሻ የህጻናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር ከእናት ባንክ ጋር በመተባበር ለድርጅቱ ሰራተኞች፣ ለወጣት ታዳጊዎች እና ከማዕከሉ እንክብካቤ አግኝተው ወደ ማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ ልጆች የፋይናንስ እውቀትን ለማጎልበት ያለመ ስልጠና አካሄደ።
ስልጠናው በዕቅድ አዘገጃጀት፣ ግብ በማስቀመጥ፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በቁጠባ እና በብድር አጠቃቀም ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ገቢያቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ፣ ለወደፊት የሚያስፈልጋቸውን ግቦች እንዲያቅዱ፣ የቁጠባ ባህልን እንዲያዳብሩ እና የብድርን ጥቅምና ኃላፊነት በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ የሚያግዝ እውቀት ለማግኘት አስችሏል።
የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ተሳታፊዎች የገንዘብ አያያዝ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ፣ በራሳቸው አቅም ላይ እምነት እንዲያዳብሩ፣ ለወደፊት ሕይወታቸው ተግባራዊ የገንዘብ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ነፃነትን ለማሳካት የሚያስችላቸውን መሠረት ማጠናከር ነው።
ዘውዲቱ መሸሻ ማህበር ለልጆችና ወጣቶች የተሻለ የወደፊት ሕይወት ለመገንባት ከመደበኛ እንክብካቤ ባሻገር የሕይወት ክህሎትን፣ የራስን አቅም ማጎልበትን እና በራስ መተማመንን በማጠናከር ላይ ይሰራል። ማህበሩ ለዚህ ትርጉም ያለው ትብብር እና ለተሳታፊዎች የፋይናንስ እውቀት ለማጎልበት ለሰጠው ድጋፍ እናት ባንክን ከልብ ያመሰግናል።
በጋራ ትብብር፣ በእውቀት እና በቁጠባ የተሻለ ነገን እንገንባ!
ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha



