አዲስ አበባ | ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም

ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር ከማዕከሉ ውጭ በቤተሰቦቻቸው ዘንድ እየኖሩ ድጋፍ ለሚያገኙ ህፃናት የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ በማቅረብ የትምህርት ሂደታቸውን ለማጠናከር ድጋፍ አደረገ።
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ህፃናቱ በትምህርታቸው የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንዲቀንሱ፣ በትምህርት ሂደታቸው የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና የተሻለ የትምህርት ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያግዝ ነው።
ድርጅታችን ህፃናት በቤተሰቦቻቸው እንክብካቤ ሥር እያደጉ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ፣ መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉ እና ወደ ተሻለ የወደፊት ሕይወት እንዲሸጋገሩ በተለያዩ የድጋፍ መርሃ ግብሮች እየሠራ ይገኛል።

ለእያንዳንዱ ህፃን የተሻለ የትምህርት ዕድል፣ ለተሻለ ነገ እንሠራለን!

#ዘውዲቱመሸሻ #የትምህርትድጋፍ #የህፃናትእንክብካቤ #ChildEducation #ChildWellbeing #BetterFuture

ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha