አዲስ አበባ | ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም
ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር አዲስ ዓመትን በማስመልከት በአካባቢው የሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ አባላት የማዕድ ማጋራትና ለበዓል የሚሆኑ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
ድርጅቱ በዓሉ ለሁሉም ሰው የደስታ፣ የተስፋና የአብሮነት ጊዜ እንዲሆን በማሰብ፣ በአካባቢው በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የተለያዩ የእርዳታ ድጋፎችን አበርክቷል።
የተደረገው ድጋፍ የአዲስ ዓመት በዓልን በክብርና በደስታ እንዲያሳልፉ ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ የእለት ተዕለት ፍጆታዎችና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን፣ ድጋፉ በተለይም በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት ተደራሽ ሆኗል።
የድርጅቱ መስራች እመበረከተ ዘውዲቱ እና ም/ስራ አስኪያጅ ቀሲስ አበባየሁ በመልእክታቸው፣ አዲስ ዓመት ማለት አዲስ ተስፋን፣ አንድነትንና እርስ በርስ መረዳዳትን የምናጠናክርበት ጊዜ ነው። በመሆኑም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በቻልነው መጠን የምንችለውን ማድረግ የሁላችንም ሀላፊነት ነው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ድርጅቱ ከህፃናት እና ቤተሰቦች ጋር በመስራት ብቻ ሳይወሰን፣ በአካባቢው የሚገኙ ተጋላጭና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመደገፍ የማህበረሰብ አብሮነትንና መረዳዳትን ለማጠናከር የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጧል።
በመጨረሻም ድርጅቱ አዲሱ ዓመት ለሁሉም የሰላም፣ የጤና፣ የተስፋና የብልጽግና ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
“አዲስ ዓመትን በፍቅር፣ በአብሮነትና በመረዳዳት እንቀበል!”
ለበለጠ መረጃና ድጋፍ ለማድረግ፦
Websit: https://zewditumeshesha.org/
Telegram: t.me/+pMFeQ3LZ-WliNmRk
YouTube: youtube.com/@ZEWDITUASSOCIATION
TikTok: tiktok.com/@zewditumesaha







